★ Use Secondary Monitor ★   Cross Reference    Verses by Topic        Show Version:       

Who we are in Christ (በክርስቶስ ያለን ማንነት)


 ቆላስይስ 2:12  በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ።
 ቆላስይስ 2:13  እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ።
 ቆላስይስ 2:3  የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።
 ቆላስይስ 2:6  እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
 ቆላስይስ 2:7  ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
 ቆላስይስ 2:9  በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።
 ቆላስይስ 2:9-10  በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
 ቆላስይስ 3:1  እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ።
 ቆላስይስ 3:10  የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።
 Go Back