Use Secondary Monitor    Cross Reference    Verses by Topic        Show Version:       
   ብሉይ ኪዳን     አዲስ ኪዳን 
Search the Bible:   
Read   Multiple Bible Versions     62 Day Bible Reading     31 Day Bible Reading    Show Selected Verses      Select All Verses     Clear Selected Verses      Clear Screen     Font Size:       Alignment:  
1
2
3
4
1. በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች። የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ መሰደባችንንም አርቅ ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
2. በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ለጌጥና ለክብር ይሆናል፥ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።
3-4. ጌታም የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፥ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፥ በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፥ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፥ ቅዱስ ይባላል።
5. እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤአቸውም ላይ በቀን ዳመናንና ጢስን በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
6. በቀን ከሙቀት ለጥላ፥ ከዐውሎ ነፋስና ከዝናብም ለመጠጊያና ለመሸሸጊያ ጎጆ ይሆናል።
 Go Back