Use Secondary Monitor    Cross Reference    Verses by Topic        Show Version:       
   ብሉይ ኪዳን     አዲስ ኪዳን 
Search the Bible:   
Read   Multiple Bible Versions     62 Day Bible Reading     31 Day Bible Reading    Show Selected Verses      Select All Verses     Clear Selected Verses      Clear Screen     Font Size:       Alignment:  
1. ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ምስጉን ነው።
2. ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3. ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
4. ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም ነው።
5. ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል።
6. ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።
7. ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።
8. በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራም።
9. በተነ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል፤ ቀንዱ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10. ኃጢአተኛም አይቶ ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፤ የኃጢአተኞችም ምኞት ትጠፋለች።
 Go Back