Online Mezmur  - Your Online Mezmur Lyrics Psa 35:28: And my tongue shall speak of Your righteousness And of Your praise all the day long. 
Home         Use Secondary Monitor     Show Version Name:      Bible Cross Reference        Bible Verses by Topic                
   ብሉይ ኪዳን     አዲስ ኪዳን 
Search the Bible:   
     Read   Multiple Bible Versions     62 Day Bible Reading     31 Day Bible Reading      Show Selected Verses       Select All Verses      Clear Selected Verses       Clear Screen     Font Size:       Alignment:  
1. አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
2. ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።
3. ሰውን ወደ ኅሳር አትመልስም፤ የሰው ልጆች ሆይ፥ ተመለሱ ትላለህ፤
4. ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ትጋት ነውና።
5. ዘመኖች የተናቁ ይሆናሉ፥ በማለዳም እንደ ሣር ያልፋል።
6. ማልዶ ያብባል ያልፋልም፥ በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።
7. እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና።
8. የተሰወረውን ኃጢአታችንን በፊትህ ብርሃን፥ በደላችንንም በፊትህ አስቀመጥህ።
9. ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመዓትህ አልቀናልና፤ ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ።
10. የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንገሠጻለንና።
11. የቍጣህን ጽናት ማን ያውቃል? ከቍጣህ ግርማ የተነሣ አለቁ።
12. በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን።
13. አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ስለ ባሪያዎችህም ተምዋገት።
14. በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን።
15. መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይለናል።
16. ባሪያዎችህንና ሥራህን እይ፥ ልጆቻቸውንም ምራ።
17. የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።
 Go Back