Online Mezmur  - Your Online Mezmur Lyrics Psa 35:28: And my tongue shall speak of Your righteousness And of Your praise all the day long. 
Home         Use Secondary Monitor     Show Version Name:      Bible Cross Reference        Bible Verses by Topic                
   ብሉይ ኪዳን     አዲስ ኪዳን 
Search the Bible:   
     Read   Multiple Bible Versions     62 Day Bible Reading     31 Day Bible Reading      Show Selected Verses       Select All Verses      Clear Selected Verses       Clear Screen     Font Size:       Alignment:  
1. አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥
2. ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።
3. ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።
4. ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ትፈርዳለህ የድሆችንም ልጆች ታድናለህ፤ ክፉውንም ታዋርደዋለህ።
5. ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኖራል።
6. እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል።
7. በዘመኑም ጽድቅ ያብባል፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።
8. ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል።
9. በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።
10. የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።
11. ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።
12. ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።
13. ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።
14. ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፤ ስማቸው በፊቱ ክቡር ነው።
15. እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።
16. በምድር ውስጥ በተራሮች ላይ መጠጊያ ይሆናል፤ ፍሬውም ከሊባኖስ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እንደ ምድር ሣር በከተማ ይበቅላል።
17. ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉም አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል።
18. ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።
19. የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘላለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።
20. የእሴይ ልጅ የዳዊት መዝሙር ተፈጸመ።
 Go Back