Use Secondary Monitor    Cross Reference    Verses by Topic        Show Version:       
   ብሉይ ኪዳን     አዲስ ኪዳን 
Search the Bible:   
Read   Multiple Bible Versions     62 Day Bible Reading     31 Day Bible Reading    Show Selected Verses      Select All Verses     Clear Selected Verses      Clear Screen     Font Size:       Alignment:  
1. ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ኢየሩሳ ትባል ነበር።
2. አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር።
3. የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፥ በዖፌልም ቅጥር ላይ እጅግ ሠራ።
4. በተራራማውም በይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን ሠራ፥ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ።
5. ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ አሸነፋቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ አሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ አሥር ሺህም የቆሬስ መሥፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ሰጡት።
6. ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።
7. የቀረውም የኢዮአታም ነገር፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
8. መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ።
9. ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም አካዝ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
 Go Back